ሩሲያ በዩክሬይኑ ጦርነት ጉዳይ በሳውዲ አረቢያ ይካሄዳል የተባለው ጉባኤ አልገባኝም እና እስኪ አስረዱኝ አለች፡፡
የሩሲያ መንግስት ጥያቄውን ያቀረበው በቃል አቀባዩ ዲሚትሪ ፔስኮቭ አማካይነት እንደሆነ ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡
ስለ ጉዳዩ ባለፈው ሳምንት በዎል ስትሪት ጆርናል ላይ ዘገባ መውጣቱ ለትውስታ ተነስቷል፡፡
በዘገባው መሰረት ምዕራባዊያን፣ እንደ ብራዚል ያሉ በማደግ ላይ ያሉ አገሮች እና ዩክሬይን የጉባኤው ተሳታፊዎች ናቸው፡፡
ሩሲያ ግን በሳውዲው ጉባኤ እንድትካፈል አለመጋበዟ ተሰምቷል፡፡
የሩሲያ መንግስት ለማንኛውም ስለ ጉዳዩ እንከታተላለን ብሏል፡፡
ይሁንና እስካሁን ጉባኤው በምን ጉዳይ እንደሚነጋገር እና ምን ግብ እንዳስቀመጠ በጭራሽ አልገባንም ብለዋል ፔስኮቭ፡፡
የኔነህ ከበደ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Kommentare