የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጥ ማሻሻያውን በሕገ ወጥ መንገድ ለመጠቀም በሚፈልጉ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ የሕግ አስፈጻሚ አካላት ርምጃ እንዲወስዱ ኃላፊነት አንደተሰጣቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።
#የማክሮ_ኢኮኖሚ ለውጡን በቁንጽል ሳይሆን በምልዐት መመልከት ይገባል ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባወጡት አጭር መግለጫ አስረድተዋል፡፡
ዓላማችን የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አካኼዳችን ድኻ ተኮር ነው ብለዋል።
የለውጥ ሥራዎቻችን ሁሉ ስኬት በባለድርሻ አካላት የተባበረ ጥረት ላይ ይመሠረታል ሲልም አክለዋል።
ይህም ምርታማነትን፣የውጭ ንግድን እና ገቢን ተባብሮ ማሳደግ ማለት ነው ብለዋል።

#የሕግ_አስፈጻሚ አካላት የለውጥ ሥራውን ባልተገባ ሕገ ወጥ መንገድ ለመጠቀም በሚፈልጉ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ ርምጃ እንዲወስዱ ኃላፊነት አንደተሠጣቸው አስረድተዋል።
የኢዲስ አበባ የአሮሚያ እና የአማራ ክልል ንግድ ቢሮዎች የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ ፖሊሲ ለውጥ ምክንያት በማድረግ ያልተገባ ዋጋ ጭማሪ በሚደርጉ አካላት ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን ይታወሳል፡፡
#የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ ፖሊሲ ለውጥ ምክንያት በማድረግ ያልተገባ የንግድ ሥርዓት በተከተሉ አካላት ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኦሮሚያ እና አማራ ክልል ንግድ ቦሮዎች አስረድተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በሸቀጦች ላይ አለአግባብና ወቅቱን ያላገናዘበ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ እና አለአግባብ ምርት ባከማቹ 71 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን ተናግሯል፡፡
የአማራ እና የኦሮሚያ ክልሎችም መሰል እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል ተብሏል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የቃላት ግድፈቶች ስላሉ ቢታረሙ መልካም ነው፡፡