የውጭ ምንዛሪ ተመኑ ከብሔራዊ ባንክ እጅ ወጥቶ ገበያ መር ከሆነ በኋላ በሰዓታት ልዩነት ውስጥ የብር የመግዛት አቅም እየተዳከመ ነው፡፡
ባንኮችም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዙበትን ዋጋ በሰዓታት ልዩነት ጭምር ከፍ በማድረግ ፉክክራቸውን ቀጥለዋል፡፡
እንዲህ ያለውና ለዋጋ ንረት ያጋልጣል የተባለው ፉክክር ማብቂያው መቼ ይሆን? የሚያስከትለውስ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚሉና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ጠይቀናል፡፡
ያነጋገርናቸው የምጣኔ ሐብት ባለሙያ ዋሲሁን በላይ ባለሞያ እንደሚሉት..
• ባንኮች የውጭ ምንዛሬ መግዣ ዋጋቸውን በሰዓት ልዩነት ከፍ እያደረጉ የሚፎካከሩት ያለችውን ውስን የውጭ ምንዛሬ ለመሰብሰብ ካላቸው ፍላጎት የተነሳ ነው፡፡
• የመግዣ ዋጋው በየጊዜው ከፍ እያለም ጣሪያው የት እንደሚደረስ ለመገመት በሚያስችግር ሁኔታ መቀጠሉ አይቀሬ ነው፡፡ እኛም እየሄድንበት ያለው መንገድ ተመሳሳይ ነው፡፡
• ናይጀሪያ አምና በIMF ምክረ ተመሳሳይ ፖለሲ ተግባራዊ አድርጋ ዘንድሮ አንድን ዶላር በ1 ሺህ 480 ናይራ እየመነዘረች ነው፡፡
• የምንዛሬ ዋጋው ተመን ከፍ ባለ ቁጥር እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ከፍተኛ የገቢ ምርት ከውጭ ለሚያስመጡ ሃገራት የዋጋ ንረቱን ጫና እያከፋው ይሄዳል፡፡
• በተለይ ቋሚ ደመወዝ የሚያገኘው በዋጋ ንረቱ ከፍተኛ ፈተና ውስጥ ሊገባ ይችላል፡፡
• የጥቁር ገበያውን ተወዳዳሪ እስከማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ እና ባንኮች በቂ የውጭ ምንዛሪ ክምችት እስኪኖራቸው ድረስ የባንኮች የውጭ ምንዛሬ የመግዣ ጣሪያ ከፍ እያለ ይቀጥላል፡፡
• በቅርቡ በቂ ክምችት ይኖራል ወይ? ጥቁር ገበያውስ ይጠፋል ወይ? የሚለው ግን አጠያያቂ ነው፡፡
Kommentare