top of page

ሐምሌ 25፣2015 - ፆታን መሠረት አድርገው ስለሚፈፀሙ ጥቃቶች ትክክለኛ መረጃ እየተገኘ አይደለም ተባለ

ጥቃቶቹ በየጊዜው ጨምረዋል ቢባልም በምን ያህል ለሚለው ትክክለኛ መረጃ እንደሌለ ተነግሯል።


ይህን የመረጃ ክፍተት ይሞላል የተባለ ፖሊሲ ኢትዮጵያ እያዘጋጀች እንደምትገኝ ሠምተናል።


ፖሊሲው ፆታን መሠረት አድርገው የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት ያግዛል ተብሎ ተስፋ እንደተጣለበት ተጠቅሷል።


መረጃውን በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች ጥቃት ጥበቃ እና ምላሽ ዴስክ ሃላፊ ወይዘሮ ህሊና ላቀው ለሸገር ነግረዋል።


ረቂቅ ፖሊሲው አሁን ላይ በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ይገኛል ብለዋል።


እስከ አሁን ፖሊሲው ባይኖርም ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው እየተሰራበት ያለውን አገር አቀፍ ስትራቴጂ በመጠቀም በሴቶች እና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ለመከላከል ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ወይዘሮ ህሊና ተናግረዋል።


ጥቃት የተፈፀመባቸው ሴቶች ይህንኑ የሚያሳውቁበት የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንዳለ የጠቀሱት ሃላፊዋ የስነ ልቦና እና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ በተቋማቸው እንደሚሰጥም ጠቅሰዋል።


በስራ ቦታ የሚፈፀሙ ፆታ ተኮር ጥቃቶች በሚያቆሙበት መንገድ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት ዛሬ በኢንተር ላግዠሪ ሆቴል ተካሂዷል።


በአዲስ አበባ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በተዘጋጀው በዚህ ውይይት በተለያዩ ተቋማት በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ለመከላከል አግዘዋል የተባሉ ተሞክሮዎች ቀርበዋል።



ንጋቱ ረጋሳ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz


Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page