top of page

ሐምሌ 24 2017 - ከቀናት በፊት በጋምቤላ ክልል በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ከ1,900 በላይ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰማ

  • sheger1021fm
  • Jul 31
  • 1 min read

ከቀናት በፊት በጋምቤላ ክልል በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ከ1,900 በላይ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰማ።


ይህን የሰማነው ከጋምቤላ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ነው።


በክልሉ የተከሰተው የጎርፍ አደጋርም ከኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ በተዘጉ የውሃ ማፋሰሻ ቱቦዎች ምክንያት እንደሆነም ኮሚሽኑ ነግሮናል።


አደጋው በቤቶችና ንብረቶች ላይ ጉዳት ቢያደርስም በሰው ላይ ግን ጉዳት አልደረሰም ተብሏል።


በንብረቶች ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን በተመለከተ ኮሚሽኑ መረጃ እያሰባሰበ እንደሆነም ነግሮናል።


የጋምቤላ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጃክ ጆሴፍ ሐምሌ 18 በጋምቤላ ዋና ከተማ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በ5 ቀበሌዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ለሸገር ተናግረዋል።


በክልሉ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ በከተማዋ እየተገነባ ባለው የኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ የማፋሰሻ ቱቦዎች በቆሻሻ መዘጋታቸው ለአደጋው መንስኤ መሆኑን ኮሚሽነሩ ነግረውናል።


በተያያዘ መረጃ የክረምቱን ዝናብ ተከትሎ የባሮ ወንዝ እየሞላ መምጣቱ ለአካባቢው ነዋሪ ትልቅ ስጋት ደቅኗል ተብሏል።


ኮሚሽነር አቶ ጃክ ጆሴፍ ከዚህ ቀደም በክረምት እየሞላ አደጋ ሲያስከትል የነበረው ባሮ ወንዝ አሁን ላይ እየሞላ በመሆኑ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ስጋት ፈጥሯል ብለዋል።


ኮሚሽነሩ አክለውም የባሮ ወንዝ እየሞላ መምጣቱን ተከትሎ በአካባቢው ያሉ ሰዎች ወደ ሌላ ቦታ እንዲሰፍሩ የጥንቃቄ መልእክት እየሰጠን ነው ሲሉም ነግረውናል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page