top of page

ሐምሌ 24 2017 - ለምግብ ምርቶች አስገዳጅ ደረጃ እንዳይወጣ የሚከላከሉ አምራች እና ነጋዴዎች መኖራቸው ተሰምቷል

  • sheger1021fm
  • Jul 31
  • 1 min read

ኢትዮጵያ ለወተት ምርት አስገዳጅ ደረጃን ካወጣች 4 ዓመት ሆኗታል፡፡


እነ እርጎ፣ አይብና ቅቤ ግን ዛሬም፣ አስገዳጅ ስላልሆኑ የወተት አምራቾች ወደ እርጎ አምራችነት እየተቀየሩ ስለመሆኑ ይነገራል፡፡


ወተትን ጨምሮ ደረጃ የወጣላቸው ምርቶች ላይም በግብይት ስርዓቱ ምቹ አለመሆን ምክንያት በሚፈለገው ልክ ቁጥጥር እየተደረገ አይደለም ተብሏል፡፡


በሌላ በኩል ለምግብ ምርቶች አስገዳጅ ደረጃ እንዳይወጣ የሚከላከሉ አምራች እና ነጋዴዎች መኖራቸው ተሰምቷል፡፡


የደረጃዎች ኢንስቲትዩት እንደሚለው ለምርቶች አስገዳጅ ደረጃን ማውጣት የሚያስፈልገው በፈቃደኝነት እንዲፈፀም የሚወጣው ደረጃ ተፈፃሚ ሳይሆን ሲቀር ነው።


የምርቱ ደረጃ አስገዳጅ ባለመሆኑ በህብረተሰብ ላይ የሚያደርሰው ተፅእኖ በሚቆጣጠረው ተቋም በጥናት ሲለይ በዚያ መሰረት ደረጃው አስገዳጅ እንዲሆን ይደረጋል ተብሏል።


አስገዳጅ ደረጃዎች በገበያው ፍትሃዊ ፉክክር እንዲኖር የሚያደርጉ ቢሆኑም አምራቾች ግን ደረጃው አስገዳጅ እንዲሆን ከማገዝ ይልቅ እንዳይወጣ የሚላከሉ እየሆኑ ነው ተብሏል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ቴዎድሮስ ወርቁ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page