የአምራቹ የስራ መስክ በሰላም እጦት እና በሌሎችም ምክንያቶች በኢኮኖሚ እድገት እና በስራ እድል ፈጠራ ያሳካል የተባለዉን ግብ እንዳላሳካ ጥናት አሳየ፡፡
ጥናቱን ያስጠናዉ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ በለሞያዎች ማህበር ሲሆን 21ኛው የማህበሩ አለም አቀፍ ኮንፈረስ ላይም ቀርቧል፡፡
ኢትዮጵያ ከግብርና ወደ ኢንደስትሪ መር ልምታደርገዉ የኢኮኖሚ ሽግግር ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው የአምራቹ ወይም ማንፋክቸሪንግ ታምኖበት የነበረ ቢሆንም በግጭት እና በተለያዩ ምክንያቶች መስኩ ግቡን ማሳካ አልቻም ተብሏል፡፡
ጥናቱን ያቀረቡት በማህበሩ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ለሜሳ ታሪኩ(ዶ/ር) የአምራቹ መስክ በኢኮኖሚ እድገት እና በስራ እድል ፈጠራ ለውጥ ያመጣል ተበሎ የነበረ ቢሆንም ያን ማሳካት እንዳልቻለ ነግረውናል፡፡
በዚህም የአምራቹ ዘርፍ በአጠቃላይ እየተፈጠረ ካለው የስራ እድል ድርሻው 5 በመቶ ብቻ እንደሆነ ጥናት አቅራቢው ለሜሳ አስርድተዋል፡፡
Коментарі