የፍልስጤሙ የጦር ድርጅት ሃማስ የፖለቲካ መሪ ኢስማኤል ሃኒያ ኢራን ውስጥ በአየር ጥቃት መገደላቸው ተነገረ።
ሃኒያ በኢራን ዋና ከተማ ቴሄራን ባለ መኖሪያ ቤታቸው የተገደሉት በእስራኤል የአየር ጥቃት ነው ሲል ሃማስ ከሷል።
ሃኒያ በቴሄራን የተገኙት በአዲሱ የኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ኤዝሽኪያን በዓለ ሲመት ላይ ለመታደም እንደነበር ተነግሯል።
አንድ ጠባቂያቸውም አብሮ መገደሉ ታውቋል። ሃማስ ለግድያው እስራኤልን ተጠያቂ አድርጓል።
ኢራን በበኩሏ በግድያው ዙሪያ ማጣራት እያካሃድኩ ነው ብላለች።
እስራኤል ግን ስለ ግድያው እስከ አሁን ያለችው ነገር የለም።

ከዚህ ቀደም ግን ለጥቅምት ሰባቱ ጥቃት በቀል ሃኒያን እና ሌሎች የሃማስ መሪዎችን ለመግደል ስትዝት እንደቆየች አሶሼትድ ፕሬስ አስታውሷል።
ሃማስ ለግድያው እስራኤልን እንደሚበቀል ዝቷል።
የኢራን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይም የሃማሱ መሪ ደም ፈሶ አይቀርም ብሏል።
መቀመጫውን በዌስት ባንክ ያደረገው የፍልስጤም አስተዳደር ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ ደግሞ የሃኒያን ግድያ አውገዘዋል።
ንጋቱ ረጋሳ
Comentarios