የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፤ ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው ስርጭት ላይ የሚገኙ 4 የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን አስጠነቀቀ።
ባለስልጣኑ 4 የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከባለሥልጣኑ ህጋዊ ፈቃድ ሳያወጡ በስርጭት ላይ መሆናቸውን አደረኩት ባለው የክትትል ስራ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
በተቆጣጣሪው መስሪይ ቤት ያለ ህጋዊ ፈቃድ በስርጭት ላይ ናቸው የተባሉ የሀይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሚከተሉት ናቸው
1. ኦሲኤን (OCN Tv)
2. ሐሪማ ቴሌቪዥን (Harima Tv)
3. ፕረዘንስ ቴሌቪዥን ( Presence Tv ) እና
4. ጀሰስ ወንደርፉል ቴሌቪዥን (Jesus Wonderful Tv )
ባለስልጣኑ ያለ ህጋዊ ፈቃድ ስርጭት ላይ ናቸው ያላቸው እነዚህ የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከሐምሌ 24 ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ፈቃድ እንድታወጡ ሲል አሳስቧል።
ይህ የማይፈጽሙ ከሆነም፤ ህጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠንቅቋል።
ባለስልጣኑ እወስዳለሁ ስላለው ህጋዊ እርምጃ ግን አላብራራም።
በአሁኑ ወቅት 43 የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ከባለሥልጣኑ ፈቃድ አውጥተው በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን
Comments