በነዳጅ የሚሰሩ የቤት አውቶሞቢሎች ላይ ተጥሎ የነበረው የውጭ ምንዛሬ ክልከላ አለመነሳቱን የገንዘብ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
በትናንትናው እለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀደም ሲል በ38 የገቢ ንግድ ሸቀጦች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ መነሳቱን መናገሩ ይታወሳል፡፡
"ቅድሚያ የማይሰጣቸው" ተብለው የተለዩ 38 ዓይነት ምርቶች ዝርዝር ውስጥ በነዳጅ የሚሰሩ የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢሎች እና ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች (የነዳጅ) ይገኙበታል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በ38 የገቢ ንግድ ሸቀጦች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ መነሳቱን በሳወቀበት በትላንቱ መግለጫ ተለይተው እግዱ ያልተነሳላቸውን ምርቶች አልጠቀሰም፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ዛሬ በወጣው መግለጫ ደግሞ በነዳጅ የሚሰሩ ሙሉ ለሙሉ ተገጣጥመው የቀረቡ የቤት አውቶሞቢል አና ባለ ሶስት እግር ተሸከርካሪዎች ላይ የተጣለው እገዳ አንደተጠበቀ ነው ብሏል፡፡
ሌሎቹ የውጪ ምንዛሬ ክልከላ ተጥሎባቸው የነበሩ ምርቶች እገዳው መነሳቱን ሚኒስቴር መ/ቤቱ በወጣው ሰርኩላር ላይ ጠቅሷል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
Comments