ሐምሌ 23፣2016 - የህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ
- sheger1021fm
- Jul 30, 2024
- 1 min read
የህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ።
ምክር ቤቱ በዕረፍት ላይ ያለ ቢሆንም የምክር ቤቱን ውሳኔ የሚሹ አስቸኳይ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ እንደሚችል በህግ ተደንግጓል፡፡
በዚሁ መሰረት ለረቡዕ ሐምሌ 24፣2016 ዓ.ም የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል፡፡
የ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በዕለቱ ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ ሪፖርት በማድረግ በአስቸኳይ ስብሰባው ላይ እንዲገኙ ጥሪ ተላልፎላቸዋል፡፡
የአስቸኳይ ስብሰባው ጉዳይ ምን እንደሆነ ምክር ቤቱ ያለው ነገር የለም።
Kommentare