በባህር ዳር ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ሀይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናግሯል፡፡
የሀይል አቅርቦቱ የተቋረጠው ከትናንት ምሽት 1፡00 ጀምሮ እንደሆነም ተቋሙ ጠቅሷል፡፡
በከፍተኛ መስመር ላይ ባጋጠመ ጉዳት ለሀይል አገልግሎት መቋረጡ ምክንያት ነው ብሏል፡፡
ጉዳት የደረሰው፤ በባህር ዳር ቁ.2 የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ በተዘረጋ 15 ኪ.ቮ ኤሌክትሪክ አስተላላፊ ኬብል ላይ መሆኑንም ተናግሯል፡፡
በዚህም፤ በአየርሀይል፣ በመኮድ፣ በአየር መንገድ፣ በውሃ ጉድጓዶች፣ በቀበሌ 14 እና 16 ባሉ ፋብሪካዎች፣ በቀበሌ 13፣ 14 እና 16 እንዲሁም በአሚኮ፣ በወገልሳ፣ በዘጌ፣ በላታ፣ በጭንባ፣ በከይባብ፣ በመራዊና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ አቅርቦት ተቋርጧል።
ተቋሙ፤ የተቋረጠውን አቅርቦት ለመመለስ ጥረት እያደረኩ ነውም ብሏል፡፡
Commentaires