top of page

ሐምሌ 22፣2016 - የኢትዮዽያ አየር መንገድ በጠቅላላው 125 አውሮፕላኖችን ባዝም ዘንድሮ የተረከብኩት ግን 5 አውሮፕላኖችን ብቻ ነው አለ።

የኢትዮዽያ አየር መንገድ በጠቅላላው 125 አውሮፕላኖችን ባዝም ዘንድሮ የተረከብኩት ግን 5 አውሮፕላኖችን ብቻ ነው አለ።


አየር መንገዱ ዘንድሮ 10 አውሮፕላን ይሰራልኝ ብሎ ቢያዝም የተረከብኩት አምስት ብቻ ነው ብሏል።


አየር መንገዱ የአውሮፕላን እጥረትና የአውሮፕላን ሞተር ባለማግኘት ግዙፍ አውሮፕላኖች ከስራ ውጪ በመሆን ፈተና እንደገጠመው ተናግሯል።


በአምራቾች ችግር ምክንያት አውሮፕላን ማግኘት አልቻልንም ሲል አየር መንገዱ አስረድቷል።


ወሬውን የሰማነው የኢትዮዽያ አየር መንገድ ዘንድሮ ምን ሰራ አፈፃፀሙስ እንዴት ሆነ ብሎ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጠበት ግዜ ተገኝተን ነው።


በአለም በጠቅላላ 4.5 ቢሊየን መንገደኞች በአየር ትራንስፖርት ተጏጉዟል የተባ ሲሆን የኢትዮዽያ አየር መንገድ 13.4ሚሊየን አለም አቀፍ መንገደኞችን አጓጉዣለሁ ብሏል ።


አመቱ ለኢትዮድያ አየር መንገድ የእድገት አመት መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።

የኢትዮዽያ አየር መንገዱ የበጀት እቅዱን ተከትሎ በዚሁ አመት 5 አለም አቀፍ የመንገደኛ መዳረሻ ኔትወርክ ዘርግቷል ተብሏል።


በጠቅላላ የኢትዮዽያ አየር መንገዱ መዳረሻውን ወደ 139 አድርሷል።


የሐገር ውስጥ ደግሞ በረራ መዳረሻዎች ደግሞ 21 መድረሱን ሰምተናል።


የኢትዮዽያ አየር መንገድ በተጠናቀቀው የስራ ዘመን 577ሺ በላይ የበረራ ሰዓቶች መብረሩን ተናግሯል።


በዘንድሮ በተጠናቀቀው የስራ ዘመን 754ሺ 681ቶን ካርጎ ጭነት ተጓጉዟል ተብሏል።


የኢትዮዽያ አየር መንገድ ይህን ሁሉ አድርጎ 7.02 ቢሊየን ዶላር ማግኘቱን ተናግሯል ።


ይህም ከ አምናው ጋር ሲነፃፀር 14 በመቶ ጭማሪ አለው ተብሏል።


ገቢው በብር 402 ቢሊየን ብር መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።


5 ቢሊየን ዶላር ከመንገደኛ የተገኘ ገቢ ሲሆን 1.65 ቢሊየን ዶላር ደግሞ ከ ጭነት የተገኘ ነው ።


የካርጎ ገቢ ቅናሽ ያደረገበት ምክንያተእ በአለም ገበያ ውድድሩ ከፍተኛ ስለሆነ ነው ተብሏል።


አየር መንገዱ 458 ሚሊየን ዶላር የሚፈጅ በጀት በፕሮጀክት ስራ ላይ ማዋሉን ተናግሯል።


ተህቦ ንጉሴ

Bình luận


bottom of page