top of page

ሐምሌ 22፣2016 - ዘንድሮ በተሰጠው የመውጫ ፈተና 22 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ አላሳለፋም ተባለ

ዘንድሮ በተሰጠው የመውጫ ፈተና 22 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ አላሳለፋም ተባለ፡፡


የግል የከፍተኛ ተቋማት በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው ተማሪዎች መካከል ያሳለፋት 13 በመቶ ብቻ እንደሆነ ተነግሯል።


ከ202ቶቹ መካከልም ከ25 በመቶ በላይ ያሳለፉት በቁጥር 29ኙ ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ካስፈተኗቸው ተማሪዎች 58 በመቶ አሳልፈዋል ተብሏል።


202 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በዘንድሮ የመውጫ ፈተና ተማሪዎቻቸውን ቢያስፈትኑም 22ቶቹ አንድም ተማሪ ማሳለፍ እንዳልቻሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ(ኘ/ር) ተናግረዋል።


ሚንስትሩ ይህን ያሉት የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የግል ኮሌጆች ዳግም ምዝገባን አስመልክቶ ከሚመለከታቸው ጋር ውይይት እያደረገበት ባለበት ወቅት ነው።


ሁሉንም በሥራ ላይ ያሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ ማካሄድ አለባቸው ተብሏል።


ማንያዘዋል ጌታሁን

Commenti


bottom of page