top of page

ሐምሌ 22፣2016 - ከዚህ ቀደም ወደ ሃገር ቤት እንዳይገቡ እገዳ ከተጣለባቸው ሸቀጦች መካከል ብስክሌቶች ተጠቃሽ ናቸው

እነዚህን ምርቶች ለሁለት ዓመታት ከውጭ ማስገባት ስላልተቻለ በገበያው ላይ እጥረት መከሰቱንና ዋጋቸውም እስከ 300 በመቶ ጭማሪ ማሳየተቱን ነጋዴዎች ነግረውናል፡፡


በኢትዮጵያ በ2013ዓ.ም በ10 ዓመታት ውስጥ ከባለ ሞተሮቹ ይልቅ ሞተር አልባ ወደ ሆኑ ተሸከርካሪዎች ለማዘንበል ስትራቴጂ ተነድፏል፡፡

ለዚህም ይመስላል በአዲስ አበባ እየተከወነ ባለው የኮሪደር ልማት ስራ ሰፋፊ የብስክሌት መንገዶች እየተገነቡ ነው፡፡ነገር ግን ሞተር አልባ የተባለው ተሸከርካሪ ገበያ ላይ እንደልብ አይገኝም ቢገኝም ዋጋው አይቀመስም፡፡


በትላንትናው እለት ብሄራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ ከዚህ ቀደም እግድ ተጥሎባቸው የነበሩት 38 ሸቀጦች ላይ የተጣለው እግድ መነሳቱን የባንኩ ገዢ ማሞ ምህረቱ ተናግረዋል፡፡


በኤሌክትሪክ ሞተር ከሚሰሩት በስተቀር የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢሎች፣ የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች እና የተገጣጠሙ ሞተር ሳይክሎችን ጨምሮ " የፍራፍሬ ጭማቂዎች እና የታሸጉ ፍራፍሬዎች የታሸጉ ውሃዎች ለስላሳ መጠጦችና አልኮል የሌላቸው መጠጦችና ሌሎችም 38 ዓይነት ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ እግድ ተጥሎ መቆየቱ ይታወሳል።


ምንታምር ፀጋው

Kommentare


bottom of page