በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጪ ምንዛሬ አስተዳደር ከባድ ቢሆንም የኢትዮጵያን
ማክሮ ኢኮኖሚ መዛባትን ለመፍታት ግን አስፈላጊ እርምጃ ነው ሲል በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ተናገረ፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ከልማት አጋሮች ጋር በመሆን ማሻሻያውን አንዲተገብርና የሀገሬወን ሀዝብ እንዲጠቀም አንዲሁም ነፃ እና ጠንካራ ኢኮኖሚ እድገት አንዲመዘገብ ኤምባሲው አበረታተለሁ ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሰት የውጭ ምንዛሪ ግብይት በገበያው አማካይነት እንዲሆን በትላንትናው እለት መወሰኑ ይታወሳል፡፡

የሽግግር ወቅት ወጪዎችንና የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ የሚያስከትላቸውን ጫናዎችን ለመቀነስ የሚረዳ 10.7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ድጋፍ ከውጭ አጋሮች ተገኝቷል ብሎ የብሔራዊ ባንኩ ተናግረዋል።
ንጋቱ ሙሉ
Comments