ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚያ ሲደርሱም የሱዳን ጦር አዛዥ ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን አቀባበል እንዳደረጉላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ተናግሯል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ፖርት ሱዳን የተጓዙት ለሱዳን መረጋጋት የሚያከናውኑት ጥረት ቀጣይ እርምጃ ነው ሲል ፅ/ቤታቸው አስረድቷል፡፡
በሱዳን በጀነራል አብድልፈታህ አልቡርሃን የሚመራው የሀገሪቱ ጦር እና አርኤስኤፍ(RSF) ከተሰኘው ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ጋር ጦርነት ማካሄድ ከጀመሩ ዓመት ከ3 ወራት ሊሆናቸው ነው፡፡

ጦርነቱ ለማስቆም አንዴ በሳውዲ አረቢያ፣ ሌላ ጊዜ በግብፅ ንግግር ለማድረግ ቢሞከርም ዘላቂ መፍትሄ እስካሁን አልመጣም፡፡
ጦርነት በተለይ በዋና ከተማዋ ካርቱም በርትቶ መቀጠሉ ይነገራል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሄዱትም በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ወደምትገኘው እና የሀገሪቱ 90 በመቶ ገቢ እና ወጪ ንግድ ወደሚቀለጣጠፍባት ፖርት ሱዳን ከተማ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Comments