top of page

ሐምሌ 2፣ 2016 - ከሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ ለነበሩና ወደ ሀገራቸው ለተመለሱ ኢትዮጵያዊያን ምን ተደረገላቸው?

ከሚያዚያ ወር ጀምሮ እስካሁን ከሳውዲ አረቢያ የተመለሱ ሰዎች ብዛት ከ57,000 በላይ ደርሷል፡፡


እነዚህ ከሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ ለነበሩና ወደ ሀገራቸው ለተመለሱ ኢትዮጵያዊያን ምን ተደረገላቸው?

በሳውድ አረቢያ እስር ቤቶች ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር የመመለሱ ስራ ከሚያዝያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም መጀመሩን ተከትሎ በአራት ወራት ውስጥ 70,000 ኢትዮጵያውያንን ለማምጣት ታቅዶ እስከ ሰኔ 29 ባለው መረጃ መሰረት ወደ ሀገር ቤት የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከ57,000 በላይ መድሳቸውን ሰምተናል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ የስደት ተመላሾች ከ2014 እስከ 2016 ባለው ጊዜ ውስጥ 4,800 የሚሆኑት የተመዘገብ ሲሆን ለ413 ብቻ የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው ተነግሮዋል፡፡


እነዚህ በፍቃደኝነት ወደ ማዕከሉ መጥተው የተመዘገቡ ናቸው የተባለ ሲሆን የአዲስ አበባ ነዋሪ ስለመሆናቸው በሚጠየቁበት ወቅት ብዙ ክፍተት እንዳለባቸው መረጃ በምቀበልበት ወቅት ገጥሞኛል ሲል መንግስት ተናግሯልል፡፡


ማርታ በቀለ


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/4mzmuzwm


Comments


bottom of page