top of page

ሐምሌ 19፣ 2016 - ከነገ ሐምሌ 20 ቀን 2016 ጀምሮ ለ3 ቀናት ብሔራዊ የሀዘን ቀን ሆኖ ታወጀ፡፡

  • sheger1021fm
  • Jul 26, 2024
  • 1 min read

ከነገ ሐምሌ 20 ቀን 2016 ጀምሮ ለ3 ቀናት ብሔራዊ የሀዘን ቀን ሆኖ ታወጀ፡፡


የሶስት ቀን የሃዘን ቀን መታወጁን የተናገሩት የሕዝብ ተወካዮች ምክረ ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ናቸው፡፡

የሶስት ቀን የብሔራዊ ሀዘን የታወጀው በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን በመሬት ናዳ ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች በማሰብ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡


በሶስት ቀኑ የሀዘን ቀን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰነደቅ ዓላማ በሁሉም አገሪቱ ግዛቶች፣ በኢትዮጵያ መርከቦች ፣ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ፅህፈት ቤቶች የሪፐብሊኩ ሰንደቀ ዓለማ ዝቅ ብሎ ይውለበለባል፡፡


በአደጋው ከ260 በላይ ሰዎች ህይወት መቀጠፉ ይታወቃል፡፡

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page