top of page

ሐምሌ 19፣ 2016 - በአዲስ አበባ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ በተፈፀመው የትዳር ፍቺዎች ወደ 5,000 የሚጠጉ ህፃናት በፈረሰ ትዳር ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል

በአዲስ አበባ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ በተፈፀመው የትዳር ፍቺዎች ወደ 5,000 የሚጠጉ ህፃናት በፈረሰ ትዳር ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል፡፡


ፍቺ በከተማዋ እየጨመረ መምጣቱንም ሰምተናል፡፡


ይህ እንደ ሀገርም ቢሆን የሚያሳድረው ጫና ቀላል አይደለም ተብሏል፡፡


አንዳንዶች ለተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ሲሉ የውሸት ፍቺን በህጋው መንገድ እንደሚፈፅሙ ተነግሯል፡፡


ከኩነት ምዝገባ አሁን አሁን የልደት ምዝገባ መሻሻል እየታየበት መሆኑ ሰምተናል፡፡


ምዝገባዎች በወቅቱ፣ በዓመት እንዲሁም በዘገየ እንደሚመዘገብ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ዳይሬክተር ዮናስ አለማየሁ ተናግረዋል፡፡


ማርታ በቀለ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page