top of page

ሐምሌ 19፣2015 - ለአፍሪካ የምጣኔ ሐብት ችግሮች በአፍሪካዊያን የተዘየዱ መላዎች ያሻሉ ተባለ

ይህ የተባለው በዛሬው እለት “መረጃ ለውሳኔ ሰጭነት” በሚል መሪ ቃል አህጉር አቀፍ ጉባኤ በኢትዮጵያ መካሄድ በጀመረበት ወቅት ነው፡፡


ጉባኤው ከዛሬ እስከ አርብ ድረስ የሚቆይ ሲሆን የተለያዩ የምርምር እና የጥናት ተቋማት እየተሳተፉበት ነው፡፡


የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ዳይሬክተር ዶ/ር አምዲሳ ተሾመ እንዲህ ያሉ ጉባኤዎች በኢትዮጵያ መካሄዳቸው የመንግስት ውሳኔ ሰጭ ተቋማት ለሚከውኗቸው ተግባራት በቂ መረጃና ማስረጃ እንዲኖራቸው ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡


ዳይሬክተሩ በኢትዮጵያ የመንግስት የተለያዩ የውሳኔ ሰጪ ተቋማት የሚወስኗቸው ውሳኔዎች ጥናት ላይ የተመረኮዙ ባለመሆናቸው የሚበዙት ስኬታማ ሳይሆኑ ይቀራሉ፤ የተሰሩ ጥናቶችንም ወደ ተግባር ለማውረድ ክስተቶች ይስተዋላሉ ተብሏል፡፡


የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት ውሳኔ ላይ ለመድረስ ወይንም ለሚከወኑት ስራ በመረጃ የተደገፉ አይደሉም ብለዋል፡፡


የሚበዙት ተቋማት በድንገት በኮሚቴዎቹ ውይይት ካደረጉባቸው በኋላ ነው ውሳኔ ላይ የሚደርሱት ይህ በመሆኑም በቂ መረጃ ባለመኖሩ ስኬታማ አይደሉም ማለታቸውን ሰምተናል፡፡



ያሬድ እንዳሻው




 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz




Kommentare


bottom of page