የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመስከረም 20፣2017 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ኤርትራ መብረር አንደማይችል ከኤርትራ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በደብዳቤ አንደተናገረው አሳወቀ፡፡
ደብዳቤው የተጻፈልኝ ሐምሌ 14፣2016 ዓ.ም ነው ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በራረው ይቋረጣል የተባለበት ምክንያት ግን አልተገለጸልኝም ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኤርትራ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ማብራሪያ እየፈለገ መሆኑን ተናግሮ ማንኛውንም ችግር በሰላማዊ መንገድ እና በፍጥነት ለመፍታት ቁርጠኛ ነኝ ሲል ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።
የኤርትራ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኞች ከመስከረም 20፣2017 ጀምሮ ወደ ኤርትራ የሚደርጉትን በረራ አንደሚያግድ የተናገረው የተጓዦች ሻንጣ ይሰራቃል፣ተደጋጋሚ የበረራዎች እና የሻንጣዎች መዘግየት ያገጥማል በሚል ምክንያት አንደሆነ ተዘግቧል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
Comments