የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት፤ ቀጠናዊ ሆኖ በአፍሪካ ህብረት በሁለት ወር ውስጥ እንዲጸድቅ ኢትዮጵያ ስምምነቱን በቅርብ ያፃደቁትን ደቡብ ሱዳን እና ብሩንዲ ሰነዱን ለህብረቱ እንዲያስገቡ የዲፕሎማሲ ስራ መስራት ይጠበቅባታል ተባለ፡፡
የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ቀጠናዊ ሆኖ እንዳይጸድቅ ግብጽ በየዓመቱ ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ ትመድባለች ተብሏል፡፡
የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት (The Nile Basin Cooperative Framework Agreement) ቀጠናዊ ስምምነት ሆኖ እንዲጸድቅ የሚያስችለውን መስፈርት ከሁለት ወር በፊት ደቡብ ሱዳን ስምምነቱን በማጽደቋ አግኝቷል፡፡
የትብብር ስምምነቱን ያጸደቁት አገራትም 6 ደርሰዋል ይህም የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ቀጠናዊ ሆኖ እንዲጸድቅ ያስችለዋል ተብሏል፡፡

ሸገር ስምምነቱ ቀጠናዊ ሆኖ ጸድቆ አለማቀፋዊ እውቅና እንዲኖረው ከኢትዮጵያ ምን ይጠበቃል ሲል ባለሙያዎችን አነጋግሯል፡፡
የአባይ ውሃ ጉዳይ ተመራማሪ የሆኑት ፈቅ አህመድ ነጋሽ፤ ኢትዮጵያ በቅርቡ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነቱን በፓርላማቸው ያጸደቁትን ደቡብ ሱዳንን እና ብሩንዲ ስምምነቱን ያጸደቁበትን ሰነድ ለአፍሪካ ህብረት እንዲያስገቡ የዲፕሎማሲ ስራ መስራት ይጠበቅባታል ብለዋል፡፡
ስምምነቱን ቀድማ የፈረመቸው እና ያጸደቀችው ኢትዮጵያ መሆኗን የተናገሩት ተመራማሪው አሁንም ከኢትዮጵያ ብዙ ይጠበቃል ይላሉ፡፡
ሰምምነቱን ስድስት አገራት ብቻ ማፅደቃቸው በቂ አይደለም ምክኒያቱም ግብጾች በየአመቱ ስምምነቱ ጸድቆ ወደስራ እንዳይገባ 10 ሚሊዮን ዶላር ይመድባሉ ያጸደቁትም ሀገራት ከስምምነቱ እንዲወጡ ይሰራሉ ያሉት ፈቃ አህመድ ኬንያም ሰባተኛ አገር ሆና ስምምነቱን እንድታጸድቅ መስራት ይጠይቃል ተብሏል፡፡
ብዙ ሀገራት ስምምነቱን ካጸደቁት የግብጽ ጫና እንደሚቀንስ ባለሙያው አብራርተዋል፡፡
ስድስት አገራት ስምምነቱን ካጸደቁት የናይል ተፋሰስ ኮሚሽን ይቋቋማል ይህ ኮሚሽን ሲቋቋም የሚሰራቸው ስራዎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ እንዲቀረጽ ማድረግ እንደሚስፈልግ የአባይ ውሃ ጉዳይ ተመራማሪ የሆኑት ፈቅ አህመድ ነጋሽ አስረድተዋል፡፡
ሌላው በጉዳዩ ላይ ማብራርያ የሰጡን የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ ቡድን የቴክኒካ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ጌዲዮን አሰፋው(ኢንጅነር) ናቸው፡፡
ሰብሳቢው ግብጽ እና ሱዳን ከትብብር ስምምነቱ አስቀደመው ነው እራሳቸውን ያገለሉት እነሱ ወደ ትብብሩ እንዲመለሱ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ስምምቱን በፓርላማ ባጸደቀችበት ወቅት ይህን እንዲስተባብር ሃላፊነቱን የተሰጠው ለውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ነው፡፡
ስምምነቱ በኢትዮጵያ ላይ የሚስከትላው ምንድነው?
ወደፊትስ በስምምነቱ የአሪቱን ጥቅም እንዴት ማስጠበቅ ይቻላል? የሚለውን ከዘርፉ ባለሞያዎች ጋር መወያየት ያስፈልጋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments