top of page

ሐምሌ 18፣2015 - ባለፈው መንፈቅ ብቻ በአትላንቲክ የውቅያኖስ መስመር ከ800 የማያንሱ ስደተኞች ሕይወት ጠፍቷል ተብሏል


በምዕራብ አፍሪካዊቱ አገር ሴኔጋል የጀልባ ተገልብጦ መስጠም አደጋ የገጠማቸው የ17 ሰዎች አስከሬን ተገኘ፡፡


አደጋው የገጠማቸው ስደተኞች ሳይሆኑ እንዳልቀረ መገመቱን አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡


2 ሰዎችን በሕይወት ማትረፍ እንደተቻለ ታውቋል፡፡


ጀልባዋ ምን ያህል ሰዎችን አሳፍራ እንደነበር ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም ተብሏል፡፡


በአትላንቲክ ውቅያኖስ የሚደረግ የስደተኞች የጀልባ ጉዞ አደጋ እየተደገገመበት መምጣቱ ይነገራል፡፡


ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከ300 በላይ ስደተኞችን አሳፍራ ከሴኔጋል የተነሳች ጀልባ የት እንደገባች መጥፋቱን ዘገባው አስታውሷል፡፡


ባለፈው መንፈቅ ብቻ በዚሁ የውቅያኖስ መስመር ከ800 የማያንሱ ስደተኞች ሕይወት ጠፍቷል ተብሏል፡፡


የነኔነሀህ ከበደ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqzComentários


bottom of page