ሐምሌ 17፣2016 - የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የስርዓተ ፆታ ፖሊሲ ሊኖራቸው እንደሚገባ ተጠቆመ
- sheger1021fm
- Jul 24, 2024
- 1 min read
የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የስርዓተ ፆታ ፖሊሲ ሊኖራቸው እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡
በኢትዮጵያ ያሉ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የስርዓተ ፆታን ሚዛን የሚያስጠብቁበት ምንም አይነት ፖሊሲ እንደሌላቸው ፎጆ ሚዲያ ኢንስቲትዩት የተባለ አለም አቀፍ ተቋም ተናግሯል፡፡ተቋሙ ሴት የሚዲያ ባለሙያዎች በየተቋማቸው የሚደርሱባቸውን ችግሮች ሊያጠና መሆኑን ጠቁሟል፡፡
ጥናቱ ችግሮቱን በመለየት መፍትሄዎቹን እንደሚያመላክትና የጥናቱ ግብም ሁሉም የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የስርዓተ ፆታ ፖሊሲ እንዲኖራቸው ማስቻል መሆኑን ለጥናቱ ግብዓት ለማሰባሰብ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ያገኘናቸው በፎጆ ሚዲያ ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ አስተባባሪ የሆኑት ኢልሃም አሊ ነግረውናል፡፡
እንደ አስተባባሪዋ አነጋገር በኢትዮጵያ በአብዛኛው ሴት ጋዜጠኞች ከወንዶች የሙያ አጋሮቻቸው አንፃር በደሞዝ ክፍያ የማነስ፣ተመጣጣኝ የስራ እድገት ያለማግኘት፣ የስራ ቦታ ላይ ፆታዊ ጥቃትና ሌሎችም ይደርስባቸዋል፤ጥናቱ ለእነዚህ ችግሮች መፍትሄዎችን ይዞ የሚመጣ ነው ብለዋል፡
Comments