top of page

ሐምሌ 17፣ 2016 - ከ6 ዓመት ወዲህ የህዝብ የመግዛት አቅም ቀንሷል ተባለ፡፡

ከ6 ዓመት ወዲህ የህዝብ የመግዛት አቅም ቀንሷል ተባለ፡፡

 

ይህን ያለው ጥናት ነው፡፡

 

ጥናቱን ያሥጠናው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ሲሆን፤ በ21ኛው የማህበሩ አለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ ቀርቧል፡፡

 

ጥናቱን ያቀረቡት በማህበሩ የጥናት እና የፖሊሲ ተንታኝ ዳይሬክተር የሆኑት ደግዬ ጎሹ(ዶ/ር) ናቸው፡፡

 

በጥናቱ መሰረት ከፈረንጆቹ 2019 ጀምሮ የህዝብ የመግዛት አቅም በእጅጉ ቀንሷል፡፡

 

ጥናቱን ያቀረቡት  ደግዬ ጎሹ(ዶ/ር) ከ2010 ጀምሮ የህዝብ ፍላጎት እየቀነሰ መጥቷል ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ ዋጋ እየጨመረ በመምጣቱ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

 

እስከ 2008 ድረስ ጥቅል ምርት እየጨመረ ነበር የተባለ ሲሆን በወቅቱ ጥቅል ምርት ከጥቅል ፍላጎት ይበልጥ ነበር ተብሏል፡፡

 

ከዚያ ወዲህ ባሉት ዓመታት ግን ጥቅል ፍላጎት፣ ጥቅል ምርትን እንደበለጠው ጥናቱ አሳይቷል፡፡

 

ያሬድ እንዳሻው



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page