top of page

ሐምሌ 17፣ 2016 - አዋሽ ባንክ በተጠናቀቀው 2016 በጀት ዓመት 11.6 ቢሊዮን ብር አተረፍኩ አለ።

  • sheger1021fm
  • Jul 25, 2024
  • 1 min read


ትርፉ ከተቀናናሽ ወይም depreciation  በፊት መሆኑን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፀሀይ ሽፈራሁ ተናግረዋል ።


የባንኩ ጠቅላላ ገቢ በ27 በመቶ እድገት በማሳየት  36.4  ቢሊዮን ብር ደርሷል ተብሏል።


የተጠናቀቀው የበጀት ዓመት"ምንም እንኳን በአለም አቀፍ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከሰቱ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የባንኩን ዘርፍ ቢፈታተኑትም አዋሽ ባንክ ከዓመት በፊት ነድፎ ተግባራዊ እያደረገ ባለው የአምስት ዓመት እስትራቴጂክ ዕቅዱ በመመራት በበጀት ዓመቱ በሁሉም ዋና ዋና የባንክ ስራ አፈጻፀም መለኪያዎች አጥጋቢ ውጤት አስመዝግቧል ሲሉ አቶ ፀሀይ አስረድተዋል።


የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ 232 ቢሊዮን  ብር ደርሷል የተባለ ሲሆን ይህም  ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ45.1 ቢሊዮን ብር ወይም በ24 በመቶ ዕድገት አሳይቷል  ተብሏል፡፡


ጠቅላላ ተቀማጩን ወደ ብር 19 ቢሊዮን ብር መድረሱም ተነግሯል።


በዓመቱ 1.5 ቢልዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማሰባሰብ  ችያለው ያለው አዋሽ ባንክ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንፃር ሲታይ የ26.8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል ብሏል፡፡


አዋሽ ባንክ በሂሳብ ዓመቱ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች በአጠቃላይ ከ37.6 ቢሊዮን ብር በላይ አዳዲስ ብድሮችን ሰጥቻለሁ ብሏል።


በተጠናቀቀዉ የሂሳብ ዓመት የባንኩ የተከፈለ ካፒታል  20.3 ቢሊዮን ብር በላይ፣ጠቅላላ ሃብቱ ደግሞ 300 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል ሲሉ ዋና ስራ አሰፈፃሚው ተናግረዋል ።

 

አዋሽ ባንክ በተጠናቀቀዉ የሂሳብ ዓመት ሁለት  ከኢትዮጵያ ምርጥ ባንክ በመባል  በግሎባል ፋይናንስ መጋዚን መመረጡን፤  ከዓለም አቀፍ ባንከሮች (International Bankers) ደግሞ ከኢትዮጵያ የዓመቱ ምርጥ ኮሜርሻል ባንክ በመባል ዕውቅና ማግኘቱን አስታወሷል።


ንጋቱ ሙሉ

Commentaires


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page