top of page

ሐምሌ 17፣2016 - በኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፣ የግል ድርጅት ሃላፊዎች እንዲሁም ጋዜጠኞች የሙስና ተሳተፊዎች መሆናቸውን ጥናት አሳየ

በኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፣ የግል ድርጅት ሃላፊዎች እንዲሁም ጋዜጠኞች የሙስና ተሳተፊዎች መሆናቸውን ጥናት አሳየ፡፡


ጥናቱ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር 21ኛው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ የቀረብ ነው፡፡


በኢትዮጵያ ሊታመኑ የሚገባቸው አካላት የሙስና ተሳታፊ መሆናቸው በጥናቱ ተለይቷል፡፡


መታመን የነበረባቸው የመንግስትን እና የማህበረሰብን ሃላፊነት የያዙ አካላት ቀጥተኛ የሙስና ተሳትፎ እንዳላቸው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ያስጠናው ጥናት አሳይቷል፡፡


ጥናቱን ያቀረቡት በማህበሩ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት አረጋ ሹመቴ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሙስና ካለባቸዉ አገራት ተርታ እንደምተገኝ አስረድተዋል፡፡


ጥናት አቅራቢዉ በሙስና ወንጀል ከፍተኝ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮች አገልግሎት የሚሰጡ የመንግስት መስሪያ ቤት የሚሰሩ ወይንም ሲቪል ሰርቫንት ተሳታፊዎች ናቸዉ ሲል ጠቁሟል፡፡


የንግድ ድርጅቶችን የሚመሩ የሰራ ሃላፊዎችም በሀገሪቱ ያለዉን የአሰራር ወጣ ወረድ አልያም ቢሮከራሲ በቀላሉ ለማለፍ በሚል የሙስና ተሳታፊዎች ናቸው ተብሏል፡፡


እነዚህ ሁሉ አካላት የሙስና ተሳታፊ የሆኑት ደግሞ ተቋማዊ አሰራር እየተፍረከረከ በመምጣቱ እና ሰራተኛው ለኑሮ የሚበቃ ገቢ ባለመኖሩ እንደሆነ ጥናት አቅራቢው ነግረውናል፡፡


ያሬድ እንዳሻው



댓글


bottom of page