በአዲስ አበባ በ2016 ዓ.ም ከ3,500 በላይ ሰዎች በፍርድ ቤት ፍቺ ፈፅመዋል ተባለ፡፡
ቁጥሩ ከአምናው በ60 በመቶ ከፍ ማለቱን የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ነው የተናገረው፡፡
በከተማዋ ከ90,000 በላይ ህፃናት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት መወለዳቸውም ተሰምቷል፡፡
2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተመዘገበው የጋብቻ ቁጥር 18,215 ሲሆን ሞት 18,752 እንዲሁም ጉዲፈቻ 169 እንደተመዘገበ ሰምተናል፡፡
ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር ፍቺ እና ልደት ብልጫ እንዳላቸው ተነግሯል፡፡
በበጀት ዓመቱ ተቋሙ ከሸርያ ፍርድ ቤት ጋር በመሆን፤ ለ835 ተጋቢዎች የጋብቻ ሠርተፍኬት እንደተሰጣቸው እና ከእነዚህ ውስጥ 8ቱ መፋታታቸውን የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ተናግረዋል፡፡
ከተጠያቂነት ጋር በተያያዘ ደግም 21 ጥቆማዎችን ተቀብለው የተቋሙን አሰራር የጣሱ ሰራተኞች እና ተገልጋዮች በአጠቃላይ 235 ሰዎች እርምጃ እንደተወሰደባቸው አስረድተዋል፡፡
ከነዋሪነት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም በዲጅታል ያልተመዘገቡ አዲስ 521,151 ነዋሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ 617,953 ነዋሪዎችን መመዝገብ ተችሏልም ብለዋል፡፡
ማርታ በቀለ
Comments