top of page

ሐምሌ 17፣2015 - አገር አቀፍ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ ነገ ማክሰኞ እና ረቡዕ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

የምክክር መድረኩ የኢትዮጵያን የግብርና፣ ቱሪዝም እና የኢኮኖሚ ዘርፎች ለማነቃቃት ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።


በመድረኩ በሚካሄዱ ውይይቶች ዘርፎቹን ለማሳደግ የሚረዱ ሃሳቦች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተጠቅሷል።


የምክክር መድረኩን የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እንደሚያዘጋጁት ሠምተናል።


መድረኩ ባለፉት 3 ዓመታት በሀገራችን በተከሰቱ የተለያዩ ችግሮች ምክንያት ተቋርጦ እንደቆየ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሃፊ አቶ ውቤ መንግስቱ ተናግረዋል።


ዋና ፀሃፊው በስካይ ላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ስለ ተነገረለት ስለዚሁ በምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ንጋቱ ረጋሳ
የሸገርንወሬዎች፣መረጃእናፕሮግራሞችይከታተሉ…https://bit.ly/33KMCqz

bottom of page