ሐምሌ 16 2017 - የሰላም እጦት በነበሩባቸው ክልሎች፤ የ2017 ትምህርት ዘመን እንዴት አለፈ?
- sheger1021fm
- Jul 23
- 1 min read
የተገባደደው የትምህርት ዘመን በሚሊየን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ያልተቀላቀሉበት፣ ተማሪዎች አንድ መፀሀፍ ለ19 እየተጠቀሙ እንዲማሩ የተገደዱበት፣ በጦርነት የወደሙ ትምህርት ቤቶች ተመልሰው ያልተጠገኑበት ዓመት ነበር፡፡
በተለይ የሰላም እጦት በነበሩባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች ትምህርትን በብዙ ውጣ ውረድ ያሳለፉ መሆኑን ሲነገር ሰምተናል፡፡
ሸገር ኤፍኤም ሬድዮ የ2017 ትምህርት ዘመን እንዴት እንደተጠናቀቀ በተለይም ሰላም እጦት በነበሩባቸው እንደ አማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ እና ሌሎችንም ለመጠየቅ ሞክሯል፡፡
በዚህም በተጠናቀቀው የትምህርት ዘመን በአማራ አምስት ሚሊዮን በትግራይ 1.2 ሚሊዮን፣ በኦሮሚያ ደግሞ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ያልተመለሱበት ዓመት ሆኖ አልፏል፡፡
በዓመቱ በሶስቱ ክልሎች የነበረውን የመማር ማስተማር ሂደትን ፈተናዎቹን በተመለከተ ጠይቀናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments