ሐምሌ 15 2017 - በህገወጥ መንገድ ወደ ተለያዩ ሀገራት የሚሄዱ ኢትዮጵያዊያን ባለፉት 5 ዓመታት ቁጥሩ ጨምሯል ተባለ
- sheger1021fm
- Jul 22
- 1 min read
በየዓመቱ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን የተሻለ ህይወት ፍለጋ አደገኛ የሆነውን የባህር ጉዞ ያቋረጣሉ፡፡
በሌላ በኩል ለህጋዊም ሆነ ለህገወጥ ስደት መንስኤ ናቸው ከሚባሉት ምክንያቶች አንዱ ነው የሚባለውን የስራ አጥነትና ድህነትን ለመቀነስ መንግስት እየሰራ መሆኑን ደጋግሞ ይናገራል፡፡
ሰዎች በህገ ወጥ መንገድ ወደ ስደት እንዳይወጡም የቅድመ መከላከል ስራ ለመስራት በተለያዩ ጊዜያት የመግባቢያ ሰነዶችን እየተፈራረመ መሆኑንም ይናገራል፡፡
በቅርቡም ውል የታሰረበት መደበኛ ባልሆነ መንገድ ከሃገር ሲወጡ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አካባቢያቸው ለመመለስ የሚያስችል የቅብብሎሽ መግባቢያ ሰነድ አንዱ ነው፡፡
በህገወጥ መንገድ ከሃገር ሲወጡ የሚያዙ ዜጎችን በመቀነስ ሰብአዊ ክብራቸውን ጠብቆ ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው እንዲመለሱና ለዘለቄታም እንዲቋቋሙ ለማድረግ የሚያስችል የቅብብሎች መግባት ሰነድ መሆኑን ተነግሮለታል፡፡
በርካታ ፍልሰተኞች በየዓመቱ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ድንበር አቋርጠው ሲወጡ በፌዴራልና በክልል የፀጥታና የህግ አካላት ለሚያዙ ዜጎች ከምግብና ከጊዜያዊ ማቆያ ጀምሮ አስቸኳይ የሆነ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ማቅረብ ፈታኝ እንደነበር በፍህት ሚኒስቴር የብሔራዊ የፍልሰት ጽህፈት ቤት ሴክሬታሪያት ኃላፊ አብርሃም አያሌው ተናግረዋል፡፡
ለዚህ ጉዳይ ተብሎ ለፀጥታና የህግ ተቋማቱ በጀት ባለመኖሩ፣ ትራንስፖርት ለማቅረብ አለመቻል፣ መውጫ እና መዳረሻ ክልሎች አብሮ አለመስራት ሂደቱን አስቸጋሪ አድርጎት ቆይቷል ተብሏል፡፡
ስለዚህም የቅብብሎሽ መግባቢያ ሰነድ መፈረሙና ከክልሎች ጋር በጋራ መስራት የሚያስችል ስምምነት መደረጉ ችግሩን ያቀለዋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments