ከ21 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን በዚህ ወቅት እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ያሳያል፡፡
ያም ሆኖ እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች በተለያዩ አካባቢዎች ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት፤ በቂ እንዳልሆነ የሚነገርለትን እርዳታ እንኳን በአግባቡ ማደረስ አልቻሉም፡፡
በግጭቶች እና በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ለእርዳታ ፈላጊነት ለተዳሩጉት፤ ለእነዚህ ሰዎች ድጋፍ እንዲደረግላቸው በተገደጋጋሚ ጥሪ ሲቀርብ ይሰማል፡፡
በሌላ በኩል የተሰበሰቡ እርዳታዎችም በትክክል ለተረጂዎች ይደርሳሉ ወይ የሚለው በብዙዎች ጥያቄ የሚነሳበት ነው፡፡
እርዳታዎቹ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች በተገቢው ተደራሽ እንዲሆን እና በሰላም ዙሪያ የሚሰሩ ስራዎችም ውጤታማ የመሆን እድላቸው ሰፊ የሚሆነው፤ ረጂ አካላት ሰንሰለት ሳያበዙ በቀጥታ ተረጂዎችን አግኝተው ማገዝ ሲችሉ እንደሆነ ይታመናል፡፡
በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ህዝብን እናግዛለን፣ እንደግፋለን ብለው የተመዘገቡ ድርጅቶች ቁጥርም ከ5,000 በላይ እንደሆኑ ተነግሯል፡፡
ለመሆኑ እነዚህ ረጂ አካላት ድጋፍም ሆነ ሌሎች በሰላም ዙሪያ ያሏቸውን የመፍትሄ ሀሳቦቻቸውን ይዘው ወደ ተጎጂዎች ድረስ ወርደው ለመስራት፤ አስቻይ ሁኔታ በሀገሪቱ አለ ወይ ስንል ሀገር በቀልና የውጭ ረጂ ተቋማት እንዲሁም የሚመለከተው አካልን ጠይቀናል፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በፍቅሩ አምባቸው
Comments