top of page

ሐምሌ 15፣ 2016 - በግብርና ዘርፍ ላይ ተሰማርተው የነበሩ 10 ባለሀብቶች በጦርነት እና በሌሎች ምክንያት ከዘርፉ ወጥተው ነበር ተባለ፡፡



ከእነዚህ ውስጥ 6 የሚሆኑት በአማራ ክልል የነበሩ ናቸው፡፡


ከ10ሩ ባለሀብቶች የተወሰኑት ብቻ መመለሳቸውን የኢትዮጵያ አበባ አትክልትና ፍራፍሬ አምራችና ላኪዎች ማኅበር ተናግሯል፡፡


የማህበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ እንዳሉት ባለሀብቶቹ ተሰማርተው የነበረው በሆልቲካልቸር የግብርና ስራ ላይ ነበር ብለዋል፡፡


ከስራ ከወጡት የተመለሱት ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው ከማለት ምን ያህሉ ወደ ስራ መመለሳቸውን በቁጥር አልተናገሩም፡፡


አሁን የግብርና ሚኒስቴር ከባለድርሻ አካላት ጋር እያዘጋጀው ያለው የ10 አመት የሆልቲካልቸር መመሪያ ባለሀብቱ በዘርፉ የተሻለ አምራችና በስፋት እንዲሰማራ የሚረዳ ነው ይላሉ፡፡


የግብርና ሚኒስቴር በበኩሉ አዲሱ የተዘጋጀው መመሪያ ከምርት ጀምሮ እስከ ምገባ ድረስ ያለው ችግርን መፍታት እንዲችል ነው፡፡



ሚኒስትር ዴኤታው መለስ መኮንን እንዳሉት በ10 አመት ውስጥ ይተገበራል የተባለው አዲሱ መመሪያ በዘርፉ አሉ የሚባሉ 22 ችግሮችን በመለየት መፍትሄዎቹን አስቀምጧል፡፡


በተለይም ዘርፉ በምርምር እየተደገፈ አይደለም ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው አሁን ዋንኛ ትኩረት ሆኖ መጥቷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡


ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም ቦታ አትክልትና ፍራፍሬ የሚበቅል ቢሆንም አዲሱ መመሪያ ግን በይበልጥ የትኛው የሀገሪቱ ክፍል ምን ዓይነት የሆልቲካልቸር ምርት በብዛት ይሰጣል የሚለው ተለይቶ እንዲሰራ እና ባለሀብቱና ገበሬው ዋነኛ ትኩረቱ በዚህ መንገድ እንዲሰራ የሚያደርግ ነው፡፡


ይህም የተሻለ ምርት ለሀገር ውስጥና ወደ ውጪም ለማቅረብ እንደሚረዳ ሚኒስትር ዴኤታው መለስ መኮንን አስረድተዋል፡፡


ኢትዮጵያ ከዚህ ዘርፍ ወደ ውጪ ምርቶችን በመላክ በአመት እስከ 6 መቶ ሚሊዮን ዶላር ታገኝበታለች የተባለ ሲሆን አዲሱ የ10 አመት መመሪያ ገቢው ወደ 3 ቢሊዮን ለማሳደግ ውጥን አለው፡፡


በረከት አካሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page