የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ እያካሄደ ባለው የምረቃ ስነስርዓት፤ ለጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ የክብር ዶክትሬት ድግሪ አበርክቷል።
ዩኒቨርስቲው ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩን የጋዜጠኝነት ተምሳሌት፣ የጋዜጠኝነት ለዛ ምልክት እና የባለታሪኮች ባለአደራ ናት ብሏል።
በተመሳሳይ ዩኒቨርሲቲው ለሆላንዳዊው ሄሪት ሆልት ላንድ በአትክልትና ፍራፍሬ ሰብል ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋፅኦ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው፡፡
በቅርቡ 60ኛ ዓመቱን ያከበረው አንጋፋው የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በልዩ ልዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ እያስመረቀ ነው፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኘ ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተማራቂ ተማሪ ወላጆች፣ የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…https://bit.ly/33KMCqz
Comments