ሐምሌ 14 2017 - ደረጃ ሳያሟሉ ለገበያ ቀርበው የነበሩ የተለያዩ ምርቶች በክትትል እንዲወገዱ መደረጋቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚ/ር ተናገረ
- sheger1021fm
- Jul 21
- 1 min read
Updated: Jul 22
የለስላሳ መጠጦች እና የጃር ውሃን ጨምሮ የተቀመጠውን ደረጃ ሳያሟሉ ለገበያ ቀርበው የነበሩ የተለያዩ ምርቶች በክትትል እንዲወገዱ መደረጋቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተናገረ።
ምርቶቹን ለገበያ ባቀረቡት ነጋዴዎች ላይ ፍቃዳቸውን ከማገድ በወንጀል እስኪጠየቁ የደረሰ እርምጃ ተወስዷልም ብሏል።
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በሀገር ውስጥ የተመረቱ እና ከውጪ የገቡ የተለያዩ ምርቶች የተቀመጠውን አስገዳጅ ደረጃ ስለሟሟላታቸው ለማረጋገጥ፤ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመትም ባለሞያዎችን በገበያዎች በማሰማራት ቁጥጥር ማድረጉን ጠቅሷል።

በቁጥጥር ስራውም ከተቀመጠው ደረጃ በታች የሆኑ የተለያዩ ምርቶች መገኘታቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ድኤታ አቶ እንዳለው መኮንን ነግረው ነግርውናል።
የአርማታ ብረት፣ የልብስ ሣሙና፣ የለስላሣ መጠጦች እና የጃር ውሃ የተቀመጠውን ደረጃ ሳያሟሉ ወደ ገበያ ተሰራጭተው ካገኘናቸው ምርቶች መካከል ናቸው ብለዋል።
ምርቶቹን ለገበያ ባቀረቡት ነጋዴዎች ላይ ፍቃዳቸውን ከማገድ በወንጀል እስኪጠየቁ የደረሰ እርምጃ ተወስዷልም ብለዋል ሚኒስትር ድኤታው።
ህብረተሰቡ ከደረጃ በታች ስለሆኑት እነዚህ ምርቶች አውቆ በመግዛት ከመጠቀም እንዲቆጠብ ለማስገንዘብ ደግሞ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እናስነግራለን ብለዋል አቶ እንዳለው።
የተቀመጠውን አስገዳጅ ደረጃ አላሟላም የተባለ እና እያንዳንዱ 1,200 ኪሎ ግራም የሚመዝን 8,84 ጥቅል የአርማታ ብረትም በዓመቱ ለገበያ እንዳይቀርብ ተደርጓል ተብሏል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/567u56/
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments