የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ6ተኛ ክፍል ውጤት ይፋ አደረገ፡፡
ቢሮው የ2016 የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ከመቶ እንዲሆን ተወስኗል ብሏል፡፡
ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 ከመቶ እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት ወስኗል፡፡
በ2016 የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85ሺ 46 በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ተማሪዎች መካከል 94 ነጥብ 3 የሚሆኑ ተማሪዎች 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ አምጥተዋል፡፡
ቀሪ 5 ነጥብ 7 ከመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ማለፊያ ነጥብ አላመጡም ሲል ትምህርት ቢሮው ባወጣው መረጃ ተመልክተናል፡፡
በረከት አካሉ
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Comments