top of page

ሐምሌ 13፣ 2016 - በእርስ፣ በእርስ ግጭት የሚዳከመው የሀገር ኢኮኖሚ

  • sheger1021fm
  • Jul 20, 2024
  • 1 min read

በተለያዩ አካባቢዎች ያለው የእርስ በእርስ ግጭት ማባሪያ አላገኘም፡፡


ችግሮችን በሰላም እንፍታ የሚሉ ድምጾች ቢሰሙም ተግባራዊ እርምጃ ግን እየታየ አለመሆኑ ግምቱ ሊቀጥል እንደሚችል ጠቋሚ ነው፡፡


ቀጣይነት ያለው የእርስ በእርስ ግጭት ደግሞ በሂደት የሌሎችን ሃገራትና ቡድኖች ጣልቃ ገብነት እያስከተለ ሌሎች የራሳቸውን ጥቅም የሚያስጠብቁበት ወደ መሆን ይሸጋገራል፡፡


እና ውጤቱም አስከፊ ሊሆን ይችላል ሲሉ ሸገር ያነጋገራቸው የፖለቲካ ሳይንስ መምህር አሳስበዋል፡፡


በግጭቱ ምክንያት ምጣኔ ሀብቱም በእጅጉ እየተጎዳ መሆኑን ጥናቶች ያሳዩ ሲሆን ግጭቱ በዚሁ ከቀጠለ የሃገርን ህልውናም ሊፈትን ይችላል ተብሏል፡፡


ያሬድ እንዳሻው



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page