top of page

ሐምሌ 13፣ 2016 - የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ እድሜ ጋብቻ የመሳሰሉ ጎጂ ባህላዊ ድርጊቶች በሴቶች በቤተሰብ ከፍ ሲልም እንደ ሃገር በብዙ የሚሰሙ መሆናቸው ይታወቃል

Updated: Jul 24, 2024

የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ እድሜ ጋብቻ የመሳሰሉ ጎጂ ባህላዊ ድርጊቶች በሴቶች በቤተሰብ ከፍ ሲልም እንደ ሃገር በብዙ የሚሰሙ መሆናቸው ይታወቃል፡፡


በአለም አቀፍ ደረጃም የሰብአዊ መብት ጥሰት ሆኖ የተፈረጀው የሴት ልጅ ግርዛት በኢትዮጵያም በተለይ ቀድሞ ባለው ጊዜ መኖሩ ታውቆ ልማዱ እንዲቀር ብዙ ሲባል ቆይቷል፡፡


እ.ኤ.አ 2016 እስከ 99 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች የተገረዙበት የሶማሌ ክልል ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዝ በቅደም ተከተል ከ91 በመቶ እስከ 73 በመቶ ሴቶችን በመግረዝ አፋር ፣ ሀረሪ ፣ ኦሮሚያ እና ጋምቤላ ክልሎች ከሁለት እስከ 5ተኛ ደረጃ ይይዛል፡፡


አዲስ አበባ ከተማም 54 በመቶ ሴቶች የተገረዙባት መሆኗን ከስምንት አመት በፊት የተጠና ጥናት ያሳየ ሲሆን እንደ አጠቃላይ ደግሞ በኢትዮጵያ የሴቶች ግርዛት 65 በመቶ ያለ እድሜ ጋብቻ ደግሞ 58 ከመቶ መሆኑን ከሴቶችና ማሀበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ያገኘው መረጃ ያሳያል፡፡


በዚህም ምክንያት በፈረንጆቹ 2025 የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለድሜ ጋብቻን ታሪክ አደርጋለሁ ብላ ስትሰራ የቆየችው ኢትዮጵያ ተሳክቶላት ይሆን ወይ ስንል የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ጠይቀናል፡፡



Comentários


bottom of page