top of page

ሐምሌ 13፣ 2016 - በምስራቅ ወለጋ ‘’ዲጋ ወረዳ’’ ለተፈናቀሉ ሰዎች እርዳታ እንዲደረግላቸው ወረዳው በድጋሚ ጥሪ አቀረበ

በምስራቅ ወለጋ ‘’ዲጋ ወረዳ’’ ለተፈናቀሉ ሰዎች እርዳታ እንዲደረግላቸው ወረዳው በድጋሚ ጥሪ አቀረበ፡፡


በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን የተፈናቀሉ ሰዎች በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ፡፡


የዞኑ አንድ ወረዳ በሆነው ዲጋ ወረዳ ብቻ ባለፉት 2 ዓመታት ተፈናቅለው በዚያው አካባቢ የሚገኙ ሰዎች ከ2,500 በላይ እንደሆኑ ሰምተናል፡፡


ከተፈናቀሉት 385 አባወራዎች መካከልም፤ 180ዎቹ ‘አርጆ ከተማ’ ውስጥ በሚገኝ አንድ የመጠለያ ጣቢያ ተጠልለው ይገኛሉ ተብሏል፡፡


የተቀሩት አባወራዎች ግን በየግለሰብ ቤቶች ተጠግተው እንደሚገኙ ከወረዳው ሰምተናል፡፡


ቀድሞ ቤት ንብረት የነበራቸው እነዚህ ተፈናቃዮቹ አሁን በችግር ውስጥ እንደሚገኙ የዲጋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ነግረውናል፡፡

ለጋሽ ድርጅቶችም የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉላቸውም ጥሪ አቅርበዋል፡፡


ተፈናቃዮቹ በምስራቅ ወለጋ ዞን፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚዋሰነው ዲጋ ወረዳ ዉስጥ ከሚገኙ 6 ቀበሌዎች የተፈናቀሉ እንደሆኑ ተነግሯል፡፡


በእነዚህ ቀበሌዎች፤ ከ2014 ጀምሮ ከ556 በለይ መኖሪያ ቤቶች በታጣቂዎች እንደተቃጠሉ መዘገባችን አይዘነጋም፡፡



ማንያዘዋል ጌታሁን ያዘጋጀውን በትዕግስት ዘሪሁን



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page