top of page

ሐምሌ 12፣ 2016  - ኢትዮጵያ ላለፉት 5 ዓመታት የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ፤ ከምስራቅ አፍሪካ አገራት ቀዳሚዋ ነች ተባለ። 

  • sheger1021fm
  • Jul 19, 2024
  • 1 min read

ወደ ኢትዮጵያ መጥተው መዋለ ነዋያቸውን እያፈሰሱ ካሉ የውጭ ባለሃብቶች ግማሽ ያህሉ ቻይናውያን መሆናቸውም ተነግሯል።

 

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የ2106 በጀት ዓመት አፈጻጸሙን እና የ2017 ዕቅዱን አስመልክቶ  ትናንት በዋና መስሪያ ቤቱ መግለጫ ሰጥቷል።

 

ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው የ2106 በጀት አመት 3.8 ቢሊየን ዶላር ካፒታል ላስመዘገቡ የውጪ እና የአገር ውስጥ ባለሃብቶች ፍቃድ መስጠቷ ተነግሯል።

 

ይህን ያህል ካፒታል ለማስመዘገቡ ባለሃብቶች ፍቃድ ስንሰጥ ከ2014 ወዲህ የዘንድሮው ከፍተኛው ነው ሲሉ፤

የኢትዮጵያ ኢንቨሰትመንት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሃና አርአያ ስላሴ የተናገሩ ሲሆን ለአመቱ ያቀድነውን ያህል ግን አይደለም ብለዋል።

 

በዓመቱ ፍቃድ ከተሰጣቸው 239 ፕሮጀክቶች 227ቱ የውጪ እንደሆኑ የጠቀሱት ዋና ኮሚሽነሯ፤ የተቀሩት በጥምረት ለመስራት የጠየቁ እና የአገር ውስጥ ባለሃብቶች እንደሆኑ ተናግረዋል።

 

የማምረቻው ዘርፍ ብዙ ባለሃብቶች ለመሰማራት ፍቃድ የወሰዱበት ነው ተብሏል።

 

አይሲቲ(ICT) ደግሞ ሁለተኛውን ደረጃ እንደያዘ ኮሚሽነር ሃና በመግለጫው ላይ ጠቅሰዋል።

 

ኢትዮጵያ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ከምስራቅ አፍሪካ አገራት ቀዳሚዋ ናት ያሉት ኮሚሽነሯ በዚሁ ለመቀጠል እንደሚሰራም ተናግረዋል።

 

በተለያዩ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ችግር የኢንቨስትመንት ፍሰቱ ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ ምንድነው?፤ በዚሁ ምክንያት ስራ አቁመው ወደ አገራቸው የተመለሱ ባለሃብቶችን በቁጥር አስደግፋችሁ ብትነግሩን ? በሚል ከጋዜጠኞች ለቀረበው ጥያቄ ደግሞ፤ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

 


ንጋቱ ረጋሣ

 


Comentários


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page