ሐምሌ 12፣ 2016 - አካባቢን በክላቹሀል የተባሉ ከ3,000 በላይ አምራች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እርምጃ ተወስዶባቸዋል ተባለ
- sheger1021fm
- Jul 19, 2024
- 1 min read
አካባቢን በክላቹሀል የተባሉ ከ3,000 በላይ አምራች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እርምጃ ተወስዶባቸዋል ተባለ፡፡
ከዚህ ውስጥ 143ቱ መዘጋታቸውን #የአካባቢው ጥበቃ ባለስልጣን ተናግሯል፡፡
የህብረተሰቡን ጤና በሚያውክ መልኩ አካባቢን ሲበክሉ በተገኙ አምራች ፋብሪካዎች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ክትትል በማድረግ ከፁሁፍ ማስጠንቀቂያ እና ከገንዘብ ቅጣት ባለፈም ተቋሙን እስከ መዝጋት የሚያደርስ እርምጃ ተወስዷል ተብሏል።
በዚህም በ143 ማምረቻ ተቋማት እንዲዘጉ ሲደረግ በ871 ማምረቻ ተቋማት፣ በ2155 አገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ እና በ6 አበባ እርሻ ልማት ላይ የማስጠንቀቂያ እርምጃ በ70 አገልግሎት ሰጪ እና ኢንዱስትሪዎች ላይ ደግሞ የገንዘብ ቅጣት ተጠሎባቸዋል ሲል ባለስልጣኑ ተናግሯል።
ፍቅሩ አምባቸው
Website: https://www.shegerfm.com/
コメント