ሐምሌ 12፣ 2016 - በአማራ ክልል የኮሌራ በሽታ በወረርሽኝ ደረጃ እየተስፋፋ መሆኑ ተነገረ፡፡
- sheger1021fm
- Jul 19, 2024
- 1 min read
በአማራ ክልል የኮሌራ በሽታ በወረርሽኝ ደረጃ እየተስፋፋ መሆኑ ተነገረ፡፡
በክልሉ 1000 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን ሰምተናል፡፡
#ኮሌራ በክልሉ በ2015 ዓ.ም በ16 ዞኖች እና በ58 ወረዳዎች በመከሰት 5000 ያህል ሰዎችን በመያዝ 90 ሰዎችን ለሞት መዳረጉ የሚታወስ ነው፡፡
ሚያዚያ 2፣ 2016 ዓ.ም ዳግም ያገረሸው ወረርሽኙ አሁን ላይ በተለያዩ የክልሉ ወረዳዎችና አካባቢዎች መዛመቱን ተነግሯል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/ys4czu59
ማርታ በቀለ
Comments