ሐምሌ 11 2017 - ''አዳዲስ ት/ት ቤቶችን በመገንባት በፈረቃ የሚሰጥ ት/ት ለማስቀረት እየሰራሁ ነው'' የአዲስ አበባ ት/ት ቢሮ
- sheger1021fm
- Jul 18
- 1 min read
የትምህርት ጥራት አለ ወይ? ለማለትም በአንድ ክፍል ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር ማየት ወሳኝ ነው የተባለ ሲሆን፤ እንደማሳያም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ በአንድ ክፍል ውስጥ 45 ተማሪዎች ብቻ መማር እንዳለባቸው ዓለም አቀፍ መስፈርት ያስገድዳል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማም በአለም አቀፍ መስፈርቱ መሰረት በአንድ ክፍል ውስጥ ከ34-39 ተማሪዎችን የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች አሉ የተባለ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች እስከ 90 ተማሪዎች በአንድ ክፍል ውስጥ እንደሚማሩ ሰምተናል፡፡

ይህንን የሰማነው አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የ2017 የትምህርት ዘመን አፈፃፀም እና የ2018 የትምህርት ዘመን ዕቅድ ላይ ከመምህራን ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው፡፡
በ2017 የትምህርት ዘመን በተሰሩ ስራዎች በፈረቃ ሲያስተምሩ ከነበሩት ትምህርት ቤቶች ውስጥ 7 የሚሆኑት የሙሉ ቀን ትምህርት እንዲያስተምሩ አድርገናል ያለው ቢሮው፤ አሁንም ቢሆን ግን አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ላይ በአንድ ክፍል ውስጥ 90 ተማሪዎች እየተማሩ እንደሆነ ተናግሯል፡፡
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ለሶስት ቀናት ይቆያል ባለው የውይይት መድረክ በ2017 የትምህርት ዘመን ያጋጥመው ችግሮች ላይ ይመክራል፤ ለ2018 የትምህርት ዘመን ደግሞ ሊሰሩ የሚገቡ ተግባራት ላይ የትምህርት ባለሙያዎች መምህራንና አመራሮች ጋር ይወያያል፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX












Comments