top of page

ሐምሌ 11 2017 - በኢትዮጵያ ከሚፀንሱ 100 ሴቶች መካከል 21ዱ ፅንሳቸውን ያቋርጣሉ

  • Jul 18, 2025
  • 1 min read

ከሚያረግዙ ሴቶች 41 በመቶዎቹ ፈልገው አይደለም የሚያረግዙት፡፡


ጽንስን በተመለከተ ኢትዮጵያ ከዛሬ 20 ዓመት በፊት ተቀብላ ያጸደቀችውና የተሻሻለው ህግ ጽንስን በህጋዊ መንገድ ማቋረጥ እንደሚቻል ይፈቅዳል፡፡


ይህ ማለት ግን ጽንስ ማቋረጥ ወንጀል አይደለም ማለት እንዳልሆነ የዘርፉ ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡


ይህ ህግ የፀደቀው ጤንነቱ ባልተጠበቀ መልኩ ጽንስን የሚያቋርጡ እናቶችን ሞት ለመቀነስ ታስቦ እንደሆነም ተነግሯል፡፡

ጽንስን በህጋዊ መንገድ ማቋረጥ የሚችሉት የአስገድዶ መደፈር ጥቃት የደረሰባቸው፣ ከዘመድጋር በተደረገ የግብረ ስጋ ግንኙነት የተፈጠረ ጽንስ፣ ከ18 ዓመት በታች የሆነች ልጅ፣ የአምሮ ወይም አካል ጉዳተኛ ከሆነች አንድ ሴት ጽንስን በህጋዊ መንገድ ማቋረጥ እንደምትችል ተፈቅዷል ሲሉ የአይፓስ ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር የሆኑት ደመቀ ደስታ(ዶ/ር) ነግረውናል፡፡


ህጉ የሚፈቅደው ይህንን ቢሆንም አሳሳቢ የሆነው የጽንስ ማቋረጥ እያጋጠመ ያለው ከተፈቀደላቸው ውጪ ያሉት ናቸው ሲሉ በጤና ሚኒስቴር የሚንስትሯ አማካሪ ሰለሞን ወርቁ(ዶ/ር) ነግርውናል፡፡


ጉዳዩም ለሴቶቹም ለሃገርም አሳሳቢ ብለዋል፡፡


አይፓስ ኢትዮጵያ የተሻሻለው ህግ 20 ዓመት መሙላቱን ተከትሎ ከተለያዩ ተቋማት ጋር መሻሻል ስላለባቸው ጉዳዮች መክሯል፡፡


ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Recent Posts

See All
በ'ፊንቴክ' የማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች ላይ ፖሊስ የጠየቀው የተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ላይ ለመወሰን ፍርድ ቤት ለነገ ቀጥሯል።

ከ"ፊንቴክ" (Fintech) ኢንቨስትመንት ጋር በተያያዘ በከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች ዛሬ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። መርማሪ ፖሊስ በቀሪ የምርመራ ስራዎች ምክንያት ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page