top of page

ሐምሌ 11 2017 - ለተቀጣሪ ሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲኖር ማድረግ እንደ አንድ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ እየታየ ነው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Jul 18
  • 1 min read

ከኢትዮጵያ ምርቶችን የሚገዙ የአውሮፓ ሀገራት እና አሜሪካ ጉዳዩን እንደ አንድ ቅድመ ሁኔታ እያቀረቡት እንደሆነ ተጠቅሷል።


ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል በኢትዮጵያ በህግ እንዲወሰን ካልተደረገ እነዚህ ሀገራት ምርቶችን ከኢትዮጵያ መግዛት ሊያቆሙ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማህበር ባዘጋጀው አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ሲነገር ሠምተናል።


የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማህበር ዛሬ ሲኤምሲ በሚገኘው መስሪያ ቤቱ ማካሄድ የጀመረው አለም አቀፍ ጉባኤ እስከ ነገ ይቆያል።

ree

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዙሪያ የተዘጋጁ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበውም ተሳታፊዎች እየተወያዩባቸው ነው።


ማህበሩ እንዲህ አይነቱን አለም አቀፍ ኮንፈረንስ ሲያዘጋጅ የዘንድሮው ለ22ኛ ጊዜ እንደሆነ ሠምተናል።


ከ34 ዓመት በፊት የተመሠረተው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማህበር አሁን ከስድስት ሺህ በላይ አባላት አሉኝ ብሏል።


ንጋቱ ረጋሣ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page