top of page

ሐምሌ 11፣ 2016 - ‘’ይህም ሆኖ ግን የትራንስፖርት አገልግሎቱ መሰረታዊ ለውጥ ሲያመጣ አላየንም’’ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በአዲስ አበበ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ለማሻሻል የተለያዩ ስራዎች ቢከወኑ ችግሩ ግን አልተቃለለም፡፡


ጉዳዩ በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ ተነስቶ ውይይት ተደርጎበታል፡፡


‘’ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ 300 በላይ ዘመናዊ አውቶብሶች እና 150 የሚደረሱ የኤሌክትክ ሚኒባሶች ገብተዋል’’ ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ‘’ይህም ሆኖ ግን የትራንስፖርት አገልግሎቱ መሰረታዊ ለውጥ ሲያመጣ አላየንም’’ ብለዋል፡፡


ሆን ተብሎ አውቶቡሶች ላይ ብልሽት እንዲያጋጥም ማድረግ፣ አውቶብሶቹን ካለ ስራ ማቆም እና ሌሎችም የአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ችግር እንዲያጋጥም እና በሚሰራው ስራ ለክ ለውጥ እንዳይመጣ አድርጎታል ብለዋ ከንቲባዋ፡፡


#የኤሌክትሪክ መኪኖችን ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ መገንባቱ ከምን ደረሰ የሚለው ደግሞ ሌላኛው ከምክር ቤቱ አባላት የተነሳ ጥያቄ ነው፡፡


የኮሊደር ልማቱ ሲከወን የኤሌክትክ መኪኖችን ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያም አብሮ እየተገነባ መሆኑን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች አበቤ አሁን ከተገነቡት ውጭ በመጭዎቹ ጊዜአትም አዳስ ጣቢያዎች ለመገንባት እቅድ ይዘናል ብለዋል፡፡


በተጨማሪም ለወደፊት ወደ ከተማዋ ለማስገባት ያሰብናቸውን ባሶች በኤሌክትሪክ የሚዘወሩ ተሽከርካሪዎች ለማድረግ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡


ዘርፉ አሁን ካለበት የበለጠ እንዲሰራ እና በሚጠበቅበት ልክ እንዲያገለግል ተሸከርካሪዎችን ከማስገባት፣ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን ከመገንባት እና በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ያሉትን ብልሹ አሰራሮች ከማረም በተጨማሪ ዘርፉን በቴክኖሎጂ በማገዝ የትራንስፖርት ፍሰቱን ለማሻሻል ስራዎች እንደሚከወኑ ተናግረዋል፡፡



ፋሲካ ሙለወርቅ



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page