በአፋርና በሶማሌ ክልል መካከል እያሰለሰ የሚፈጠር ግጭት ለንጹሃን ሞትና መፈናቀል ምክንያትት ሆኖ የዘለቀውን ለማቆም ሁለቱ ክልሎች መስማማታቸው ተናግረዋል፡፡
በይዞት ይገባኛል ጥያቄ ምክንያት በተደጋጋሚ ግጭት ከሚነሳባቸው ግጭቶች መካከል የአፋርና የሶማሌ ክልሎች ይገኙበታል፡፡
ክልሎቹ ዛሬ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት መግለጫ ተኩስ ለማቆም መስማማታቸው ተናግረዋል፡፡
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አወል አርባ ‘’ግጭት ለማቆም ተስማምተናል’’ ብለዋል፡፡

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሀመድ በበኩላቸው በሁለቱ ክልሎች መካከል ለንጹሃን ሞትና መፈናቀል ምክንያት የሆነው ግጭት ለማቆም ‘’በፌዴራል ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች በተሰጠው ውሳኔ ከስምምነት ተደርሷል’’ ብለዋል፡፡
ሙስጠፌ መሐመድ ባለፉት ዓመታት ጀምሮ የነበረው ግጭት ለሰው ሕይወት መጥፋትና ላላስፈላጊ ውድመት ምክንያት ሆኖ ቆይቷል ብለዋል፡፡
አሁን ግን ይህን ግጭት ለመፍታት ሁለቱ ክልሎች መስማማታቸውን ተናግረዋል፡፡
በስምምነቱ መሰረትም ግጭቶች እንዲቆሙና የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ ከስምምነት ተደርሷል ብለዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Website: https://www.shegerfm.com/
Comments