ሐምሌ 11፣ 2016 - የሆልቲካልቸር ዘርፍ ከአምናው 123 ሚሊን ዶላር ቅናሽ አለው ተብሏል
- sheger1021fm
- Jul 18, 2024
- 1 min read
የሆልቲካልቸር ዘርፍ በዚህ ዓመት ያስገኘው የውጪ ምንዛሪ ገቢ ከአምናው ያነሰ ነው፡፡
ገቢው ከአምናው 123 ሚሊን ዶላር ቅናሽ አለው ተብሏል፡፡
ይህንን ያሉት የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ ናቸው።
ሚኒስትሩ እንዳሉት በዚህ ዓመት የሆልቲ ካልቸር ምርቶች ወደ ውጪ በመላክ 535 ሚሊዮን ዶላር አስገኝቷል ባለፈው ዓመት ግን 658 ሚልየን ዶላር ገቢ ተገኝቶ ነበር።
ዘርፉ ከቡና በመቀጠል ሁለተኛው የውጪ ምንዛሪ አስገኚ ቢሆንም የተለያዩ ችግሮች ይታዩበታል ብለዋል።
ይህንን ለማስተካከል ብሔራዊ የሆልቲካልቸር #ረቂቅ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው ተብሏል።
ወደ ውጪ ከሚላከው የሆልቲካልቸር ምርት፤ አበባ በገቢ ቅድሚያ የሚይዝ ሲሆን ከፍራፍሬ የሚገኘው ገቢ ከ100 ሚልየን ዶላር አይበልጥም ተብሏል።
ኢትዮጵያ በዘርፉ ከፍተኛ አቅም ቢኖራትም ለዘርፉ የሚሰጠው የፋይናንስ አቅርቦት አንስተኛ መሆን፤ መሰረተ ልማት አለመሟላት፤ የገበያ መረጃ እጥረት ችግር እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ክልሎች ላይ ለአልሚዎች በፍጥነት መሬት አለማስተላለፍ ችግር ይታያልም መባሉን ሰምተናል።
Comments