top of page

ሐምሌ 11፣ 2016 - ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ጅቡቲ በዓመት ከውጪ ሀገራት ከ21 ሚሊዮን ዶላር በሚበልጥ ገንዘብ የዶሮ ስጋና እንቁላል ወደ ሀገራቸው ያስገባሉ ተባለ

  • sheger1021fm
  • Jul 18, 2024
  • 1 min read

ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ጅቡቲ ከፍተኛ የዶሮ ሀብት ባለቤቶች ቢሆኑም በዓመት ከውጪ ሀገራት ከ21 ሚሊዮን ዶላር በሚበልጥ ገንዘብ የዶሮ ስጋና እንቁላል ወደ ሀገራቸው ያስገባሉ ተባለ፡፡


የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት የእንስሳት ሀብትና ገበያ ጥናት ከፍተኛ አማካሪው አመሃ ሰብስቤ ለሸገር እንደተናገሩት በተለይም በኢጋድ አባል ሀገራት ውስጥ ያለው የዶሮ ሀብት ልማትን እንደ አማራጭ የገቢ ምንጭ ለመጠቀም በጋራ መተባበር አስፈላጊ መሆኑን ነው፡፡


የኢትዮጵያ፣ የደቡብ ሱዳን፣ የኬንያ ፣የሶማሊያ እና የጅቡቲ ከፍተኛ ባለሞያዎች የተገኙበት በዶሮ ሀብት ዙሪያ የሚመክር ጉባኤ በአዲስ አበባ ትናንት መከፈቱ ተነግሯል፡፡

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page